70 likes | 289 Views
፩ . ኤነርጂ እና ማ ጓጓ ዣ. ፩ .1 የኤነርጂ ምንጮች. የድንጋይ-ከሰልን እንደ አንድ የኤነርጂ ምንጭ መጠቀም
E N D
፩. ኤነርጂ እና ማጓጓዣ ፩.1 የኤነርጂ ምንጮች የድንጋይ-ከሰልን እንደ አንድ የኤነርጂ ምንጭ መጠቀም የድንጋይ-ከሰል እንደ ዋና የኤነርጂ ምንጭነት እንጨትን በ1890ዎች ውስጥ ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ተካ፡፡ በድንጋይ-ከሰል ነዳጅነት ኃይል አንድ ጄኔረተር ኤሌክትሪክ እንዲያፈልቅ አድርጎ በእንፋሎት የሚሠራው የመጀመሪያው ፋብሪካ በ1882 ተገነባ፡፡ በ1884 ቻርለስ ፓርሰንስ ይበልጥ ውጤታማውን ባለ ከፍተኛ-ፍጥነት የእንፋሎት ተርባይን ሠራ፡፡ በ1920ዎች ውስጥ የድንጋይ-ከሰል ዱቄት ውጤታማነት ጨመረ እና ለቃጠሎ የሚያስፈልገውን አየር ቀነሰ፡፡ በ1940 አውሎ-ነፋስ እቶን (cyclone furnace) በባለ ዝቅተኛ-ደረጃ የድንጋይ-ከሰሎች በመጠቀም ያነሰ አመድ እንዲቀር አደረገ፡፡ በቅርቡ ደግሞ ኬሚካዊ ቴክኖሎጂ ኃይልን ለማውጣት እና ሥነ-ምሕዳራዊ ብክለትን ለመቀነስ የከልም (የድንጋይ-ከሰል ማእድን ተረፈ-ቁስ) አስገኘ፡፡ ቻርለስ ፓርሰንስ የፓርሰንስ የእንፋሎት ተርባይን (1907) የቤንዚን አሰሳ እና ምርት በ1901 ግዙፉ ባለ ማጠንጠኛ-አናት (spindletop) የነዳጅ-ዘይት መስክ ቴክሳስ ውስጥ መገኘት እና የኦቶሞቢል መፈብረክ ቤንዚንን በ1951 እንደ ነዳጅ ዋና ምንጭነት ከድንጋይ-ከሰል አስበለጡት፡፡ የተለያዩ ኬሚካዊ ደቂቃንን በመለያየት ድፍድፍ ነዳጅ-ዘይትን የማጣራት ኬሚካዊ ቴክኖሎጂ ከቀላል የከባቢያዊ-አየር ማጣራት ጀምሮ እና ወደ ወና (የተቀነሰ ግፊት) ማጣራት፣ ብሎም ወደ በሙቀት ማንቃቃት (thermal cracking) እና በማብላያ ወደ መጠቀም በመሸጋገር ተከታታይ መሻሻሎች አሳየ፡፡ ለቀዳማይ የድፍድፍ ነዳጅ-ዘይት ዳግም-ግኝት ሂደት ኬሚስትሪ በኬሚካሎች እና በእንፋሎት በመጠቀም ለአልማዝ መሰርሰሪያዎች፣ ለጭቃ መሰርሰሪያዎች እና ለለዳጅ-ዘይት-ከቋጥኝ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው፡፡ የሁለተኛ-ደረጃ ዳግም-ግኝት ሂደቶች ደግሞ ባለ ከፍተኛ-ግፊት ጋስ (ካርቦን ዳይኦክሳይድ) ወይም የውሃ ውህዶችን ወደ ምድር መንፋትን ይጨምራሉ፡፡ የኑክሌር ኤነርጂ የመጀመሪያው የኑክሌር ማብላያ በ1942 የተሠራው ለወታደራዊ ጠቀሜታ ነበር፡፡ የኑክሌር ቴክኖሎጂን የኤሌክትሪክ ኃይልን ማፍለቅ ጨምሮ ለሠላማዊ ጠቀሜታዎች ማዋል በ1951 የተጀመረው ደግሞ በፕሬዚዳንት አይዘንአወር አቶሞችን ለሠላማዊ መርሐ-ግብር ነበር፡፡ ኬሚስትሪ ከእዚያን ጊዜ አንስቶ በማብላያዎች ውስጥ እንደ ነዳጅ የሚጠቅሙትን ሬዲዮአክቲቭ ቁሶችን እና የኒውትሮኖችን ፍሰት ከሬዲዮአክቲቭ ብስበሳ የሚታደጉትን የማብላያ መቆጣጠሪያ ዘንጎችን በማምረት፣ የባከኑ የነዳጅ ዘንጎችን መልሶ-በማቀነባበር፣ ውድቅዳቂዎችን በማስወገድ፣ ሥነ-ምሕዳርን በማስጠበቅ እና ለጨረራ የመጋለጥን ጎጂ ውጤቶችን በመቀነስ ረገድ ጉልህ ሚና ነው የተጫወተው፡፡ አማራጭ የኤነርጂ ምንጮች ነፋስን፣ ሃይድሮኤሌክትሪክን እና የከርሰ-ምድር-ሙቀትን ከመሳሰሉት አረንጓዴ የኃይል ማፍለቂያ ዘዴዎችን መጠቀም ድርሻቸው ከዓለም ድምር የኃይል ፍልቀት አንድ ከመቶ ብቻ ይሁን እንጂ፣ በምጣኔሃብት እና በተደራሽነት እንደተመሰከረው የሚጫወቱት ሚና ፋይዳ እየጎላ ነው የመጣው፡፡በኬሚስትሪ አማካኝነት ለቴርማል እና ለፎቶቮልታይክ የጸሐይ ገበቴዎች (solar panels)፣ ለነፋስ ጄነረተሮች ክብደተ-ቀላል ካርቦን ፋይበር ውልብልቢቶች፣ ለሃይድሮኤሌክትሪክ ተክሎች ኮንክሪት እና የብረት ተርባይኖች፣ ጂኦቴርማል ምንጮችን ለማቆር ዝገት-ተቋቋሚ ተሠርተው ይገኛሉ፡፡
፩. ኤነርጂ እና ማጓጓዣ ፩.2 ኤሌክትሪካዊ የኤነርጂ ማከማቻ እና ተንቀሳቃሽ የኃይል ምንጮች አንዴ-ጠቀም ባትሪዎች የኤሌክትሪካዊ ኤነርጂ ማከማቻ በ1700ዎች ውስጥ በአሌሣንድሮ ቮልታ ከተፈለሰፈ ወዲህ ለባትሪ ኃይል ተከታታይ መሻሻሎች አስተዋጽኦ ያደረገው ኬሚስትሪ ነው፡፡ በ1890 የተሠራው ካርቦን-ዚንክ ደረቅ ባትሪ ቀዳሚውን የሌክላንሼ ‘እርጥብ ባትሪ‘ አሻሻለ፡፡ ይህ ለእጅ-ባትሪ ጥቅም እንዲውል ለንግድ የተመረተው ባትሪ እስከ ዛሬም ድረስ ከገበያ አልወጣም፡፡ በ1949 ለተለምዷዊው ባትሪ የተሠራው አዲሱ የአልካላይን ልቁጥ የባትሪውን እድሜ ከማራዘሙም ሌላ አናሳም ሆነ፡፡ ይህ አልካላይንባትሪ በእጅ ለሚያዙ የኤሌክትሮኒክስ መሣሪያዎች እና መቅረጸ-ምስሎችም ጥቅም ላይ ለመዋል ጊዜ አልፈጀበትም፡፡ ከእዚያን ጌዜ ወዲህ የተመረቱት አዳዲሶቹ የባትሪ ዓይነቶች ደግሞ በሲልቨር ኦክሳይድ፣ በሜርኩሪክ ኦክሳይድ ወይም በሊቲየም ይጠቀማሉ፡፡ ካርቦን-ዚንክ ደረቅ ባትሪ ዳግም-ተሞይ ባትሪዎች በ1859 ለንግድ የተሠራው የእርሳስ-አሲድ ዳግም-ተሞይ ባትሪ ኤሌክትሪክ ለማምረት በቁጥጥር ስር በዋለ ኬሚካዊ ብልልት በመጠቀም ረገድ ቀዳሚው ምሣሌ ነበር፡፡ በ1881 ውስጥ የተሻሻለው እና ከእዚያን ጊዜ ወዲህ በተከታታይ እየዘመነ የመጣው የእርሳስ-አሲድ ባትሪ ለኦቶሞቢሎች እና ለካሚዮኖች በአንጋፋነት ጥቅም እየዋለ ነው፡፡ በመጀመሪያ በ1899 የተፈበረከው የኒኬል-ካድሚየም ዳግም-ተሞይ ባትሪ ገበያ ውስጥ ለመወዳደር ዋጋው በጣም ወድ ነበር፡፡ ዘመናዊ ግኝቶች የሚያተኩሩት ደግሞ በሊቲየም ላይ ነው፡፡ በ1980ዎች ውስጥ በሊቲየም ብረት ለመጠቀም የተደረገው ሙከራ ከከሸፈ በኋላ ሊቲየም-አየን ባትሪዎች አሁን ለተንቀሳቃሽ-ስልኮች እና ለተንቀሳቃሽ-ኮምፒዩተሮች እነደ ልብ ጥቅም እየሰጡ ናቸው፡፡ ዳግም-ተሞይ ባትሪዎች
፩. ኤነርጂ እና ማጓጓዣ ፩.3 የመንገዶች እና የድልድዮች ቁሶች ኮንክሪት የ1950ዎች የዩናይትድ ስቴትስ የበይነ-መስተዳድር ግንባታ ውጥኖች ለመንገዶች እና ለድልድዮች ግንባታ በኮንክሪት ጥንካሬ እና ዕድሜ ላይ በእጅጉ ጥገኞች ነበሩ፡፡ በመጀመሪያ በ1824 የተሠራው እና በ1877 በፈረንሣዊው ጆሴፍ ሞኒየ እንደ ተጠናከረ ኮንክሪት በባለቤትነት የተመዘገበው የፖርትላንድ ሲሚንቶ የሲሚንቶው ልቁጥ በክፍተቶች እና በሌሎች ማጠናከሪያዎች መካከል በመሙላት ውስብስብ ኬሚካዊ አጸፌታ በማስከተል ረገድ ችግር ነበረበት፡፡ ዕድሜው እና ጥንካሬው የሚወሰነው የሲሚንቶ ፍብረካውን ሂደት በጥንቃቄ በመቆጣጠር ነው፡፡ በመጀመሪያው የኮንክሪት ድብልቅ ውስጥ የተለያዩ ኬሚካሎች በመጨመር መኮማተርን ለመቀነስ እና የዝገት ተቋቋሚነትን ለማሻሻል ይቻላል፡፡ አስፋልት አስፋልት በዋጋው እና በውጤታማነቱ ሳቢያ ለመንገድ ግንባታ የሚፈለግ ቁስ ነው፡፡ ተፈጥሯዊ አስፋልት በ1595 የተገኘ ይሁን እንጂ፣ እስከ 1902 ድረስ ከድንጋይ-ከሰል ሬንጅጋር የተያያዘ እና መንገዶችን ለመደልደል ጥቅም ላይ የሚውል አልነበረም፡፡ የቤንዚን ማጣራት ሂደት ጥጥር ወይም ከፊል-ጥጥር ዝቃጭ፣ ቢቱሜን መንገዶችን ለመደልደል ወዲያውኑ ተፈጥሯዊ አስፋልትን ተካ፡፡ በቅርቡም ውጤታማነትን እና ዕድሜን ለማሻሻል ረጋ-ሠራሽ ፖሊመሮች (synthetic polymers) ተጨመሩ፡፡ ከባድ ሸክሞችን እና አዋኪ የአየር ሁኔታዎችን ለመቋቋም የሚችሉ ልእለ-ድልዳሎች (superpave)፣ ማለትም ልእለ ውጤታማ አስፋልት መንገዶች ደግሞ የዘመኑ ቴክኖሎጂ በረከቶች ናቸው፡፡ ብረታ-ብረቶች እና ድብልቅ-ማእድናት (Metals and Alloys) የአረብ-ብረት (steel) በቀላል ክብደቱ፣ በጥንካሬው፣ በመቆያ ጊዜው፣ በቀላል አጠጋገኑ እና አገነባቡ፣ በዝቅተኛ የመትከያ ወጪው፣ ብሎም ርእደ-ምድርን የመሳሰሉትን ተፈጥሯዊ ውድመቶች በመቋቋሙ ምክንያት ለድልድዮች ዓቢይ መዋቅራዊ ቁስ እየሆነ ነው የመጣው፡፡ በ1990ዎች ውስጥ ለገበያ የዋሉት አዳዲስ ባለ ከፍተኛ-ውጤት የአረብ-ብረቶች ክፍተኛ ጥንካሬ እና ዝገት ተቋቋሚነት አላቸው፡፡ በድልድይ ግንባታ ውስጥ የአረብ-ብረትን ለመከላከል ሌላው ቴክኖሎጂ ደግሞ አሉሚኒየም ወይም ዚንክ ለ30-ዓመት የመከላለያ ልባስነት በጸዳ የአረብ-ብረት የውጭ አካል ላይ የሚረጩበት ሜታላይዚንግ ተብሎ የሚታወቀው ሂደት ነው፡፡ የጥበቃ እና የጥገና ቴክኒኮች በሁሉም የአየር ዓይነቶች ውስጥ የጎላ ጉዳት ሳይኖር እና የረጅም ጊዜ አገልግሎት ለመስጠት የመንገድ ታሕታይ-መዋቅር መጠበቅ አለበት፡፡ በመገንቢያ እና በመጠበቂያ ቁሶች ረገድ የተመዘገቡት ፈጠራዎች በመንገዶች ግንባታ መካከል ረጅም ክፍተቶች እንዲኖሩ አስችለዋል፡፡ የኮንክሪት መለሰኛዎች፣ አስፋልት እና የአረብ-ብረት የመንገድን ዕድሜ ለማራዘም የጎላ ፋይዳ አላቸው፡፡ ሌሎች ኬሚካዊ እና ፖሊሜሪክ ቁሶች የአስፋልት መንገዶችን ውጤታማነት ለማጎልበት እንደ አቆራኝ ማጣበቂያዎች ይሠራሉ፡፡ ለምሳሌ፣ ስታይሪን-ቢዩታዳዪን-ስታይሪን መቦርቦርን እና ስንጥቃትን ለመቀነስ የሚረዱ ናቸው፡፡
፩. ኤነርጂ እና ማጓጓዣ ፩.4 ፔትሮኬሚካል ነዳጆች ቤንዚንን ከድፍድፍ ነዳጅ-ዘይት ማምረት የቤንዚንን ከድፍድፍ ነዳጅ-ዘይት መገኘት ለማሻሻል ማጣሪያዎች በመጀመሪያ በሙቀት በመጠቀም ቴርማል ክራኪንግ (1913) ተብሎ በሚጠራው ሂደት የከባድ ነዳጅ-ዘይት ቅንጣትን ትላልቅ ሞሊኪዩሎች ቤንዚን ውስጥ ወደ'ሚገኙት ትናንሽ ሞሊኪዩሎች ይሰባብሯቸው ነበር፡፡ ከፍተኛ ሙቀቶች የማይፈለጉ ተረፈ-ውጤቶችን ጭምር ስለሚያስከትሉ በዝቅተኛ ሙቀቶች የሚሠራው የወና ማጣሪያ ሂደት በ1928 ጥቅም ላይ ዋለ፡፡ ንቃትን በከፍተኛ ሙቀቶች ከማግኘት ይልቅ በቦዛኝ አብላይ (inert catalyst) [በአንቂ አብላይ (catalytic cracking)] መጠቀም በ1936 በኢዩዠን ሆድሪ ተፈልስፎ በ1937 ለገበያ ወጣ እና የቤንዚን ማጣሪያ ሂደትን በስር-ነቀልነት ለወጠ፡፡ የነዳጅ-ዘይት ማጣሪያ የነዳጅ ተዳማሪዎች የቀድሞ ኦቶሞቢል ሞተሮች በባለ ዝቅተኛ ጥራት ቤንዚን በተጠቀሙ ቁጥር ብልሽት ይገጥማቸው ነበር፡፡ ሞተሮች በምቾት እና በእርጋታ እንዲሠሩ በ1921 ቲትሬቲል ሌድ ቤንዚን ውስጥ መጨመር ተጀመረ፡፡ በ1926 የቤንዚንን ጥራት ለመለካት የኦክቴን ምጣኔ ሥራ ላይ ዋለ፡፡ በሥነ-ምሕዳራዊ እሳቤ ምክንያት የእርሳስ ተዳማሪዎች (lead additives) ጥቅም ላይ መዋል በ1970ዎች ውስጥ ተቋረጠ፡፡ ዛሬ የኦክቴን ምጣኔን ለማሻሻል እና የቢንዚንን ውጤታማነት ለማጎልበት (metal deactivators)፣ ብሎም የሞተርን ዕድሜ ለማራዘም (detergents) የሞተርን ሰበቃ እና እርጅና ለመቀነስ መጠናቸው አነስተኛ የሆነ ኬሚካሎች (አልኮሆሎች፣ ኤተሮች፣ ወዘተ.) ቤንዚን ውስጥ ይጨመራሉ፡፡ በአንዳንድ አካባቢዎች ደግሞ በመልክአ-ምድራዊ ተጽእኖ ሳቢያ የነዳጅ መስመርን መቀዝቀዝ ለመታደግ ሜታኖልን የመሳሰሉ ተዳማሪዎች ይጨመራሉ፡፡ ማብላያ ለዋጮች የካርቦን ሞኖክሳይድን እና የሃይድሮካርቦንን ልቀቶች ለመቆጣጠር በ1975 ባለ ሁለት-እርከን ማብላያ ለዋጮች (catalytic converters) ተሠሩ፡፡ ብዙም ሳይቆይ ደግሞ ናይትሮጂን ኦክሳይዶችን ከጭስ-ማውጫ ለማጽዳት ሶስተኛው እርከን ታከለበት፡፡ ማብላያ ለዋጮች የሚሠሩት በብረቱ ዙሪያ ለወትሮው በፕላቲኒየም ማብላያለተከታታይ ኬሚካዊ አጸፋዎች መንስኤ በመሆን ነው፡፡ ናይትሮጂን ኦክሳይዶች ወደ ናይትሮጂን እና ኦክሲጂን ጋሶች፣ ካርቦን ሞኖክሳይድ ወደ ካርቦን ዳይኦክሳይድ ይለወጣሉ፣ ብሎም ያልተቃጠሉ ሃይድሮካርቦኖች ወደ ውሃ እና ካርቦን ዳይኦክሳይድ ይለወጣሉ፡፡ ባለ ሦስት እርከን ማብላያ ለዋጭ
፩. ኤነርጂ እና ማጓጓዣ ፩.5 ኦቶሞቲቭ ተሽከርካሪዎች ለቅያስ፣ ለምቾት እና ለደኅንነት የተራቀቁ ቁሶች የ21ኛው ምእት-ዓመት ኦቶሞቢል በቅያሱ፣ በምቾቱ እና በደኅንነቱ ለተጓጓዦች ከቀዳሚው ዘመን ጋር የሚመሳሰለው በጥቂቱ ብቻ ነው፡፡ ከፍተኛ-መብራት ፈንጣቂ የፊት-አምፖሎች በምሽት ጊዜ ጉልህ ብርሃን አላቸው፡፡ ዝገትንም በልዩ መለሰኛዎች እና ቁሶች እጅጉን ቀንሶ እናገኘዋለን፡፡ ኬሚካዊ አቀዝቃዦች በተዘጋ ምሕዳር ሥርዓት ውስጥ ይዘዋወራሉ፡፡ የኦቶሞቢል ደህንነት መስታወት መግጠም የተጀመረው በ1914 ነበር፡፡ ዛሬ ክብደትን እና የውጭ ድምጽን ለመቀነስ፣ ብሎም ብርቅርቅታን እና ልእለ-ሃምራዊ ጨረራን (ultraviolet radiation) ለመቀነስ መስታወቶች በልዩ ፖሊመሮች ይሸፈናሉ፡፡ ከደኅንነት ፈጠራዎች መካከል በወንበር ቀበቶዎች ውስጥ (በ1960ዎች ውስጥ እስገዳጅ የሆኑት) እና በአየር ከረጢቶች ውስጥ (በ1996 አስገዳጅ የሆኑት) ፖሊመር ፋይበርስ ይጠቀሳሉ፡፡ ፕላስቲክ ተገጣጣሚዎች ከብረት ወደ ፕላስቲክ በመተላለፍ የመኪኖችን ክብደት ለመቀነስ እና አዳዲስ ከፍተኛ ውጤት-ሰጪ ቁሶችን ለመለየት የተቻለው በኬሚካዊ ግኝቶች ነው፡፡ ከ፪ኛው የዓለም ጦርነት በኋላ ኦቶሞቢል ፈብራኪዎች በጥንካሬአቸው፣ በድድርነታቸው እና በአየር ሁኔታ ተቋቋሚነታቸው ምክንያት ለማይተጣጠፉ መዋቅራዊ ተገጣጣሚዎች በረጋ-ሠራሽ መሠረተ-ቤንዚን ፖሊመሮች መጠቀም ጀመሩ፡፡ ከ1970ዎች የኤነርጂ ቀውስ በኋላ ደግሞ የነዳጅን ውጤታማነት ለማሻሻል ለብረታ-ብረቶች ክብደተ-ቀላል አማራጮች ተፈለጉ፡፡ [የአማራጮቹ] ቅየሳ አተገባበሮች የሚከተሉትን ያካትታሉ፡- በኢንጄክሽን ቀረጻ የተገነቡ ውስብስብ የኣካል ቅርጾች፣ ቴርሞፕላስቲክ የግጭት-መከላከያዎች፣ ቀለሞቻቸው የማይደበዝዙ ፖሊፕሮፒሊን ፋይበሮች እና ልእለ-ሐምራዊ ጨርራ (ultra-violet) መከላከያዎች፣ ብሎም ልዩ ቀለማት፣ ልባሶች እና አጣባቂዎች፡፡ ፖሊፕሮፒሊን ፋይበሮች የጎማ ቴክኖሎጂ ተፈጥሯዊ የጎማ ምርቶች በ1800ዎች መጀመሪያ ውስጥ ይታዩ እንጂ፣ በሞቃት ወይም በቀዝቃዛ የአየር ሁኔታዎች ውስጥ በመለስለሳቸው ወይም በቀላሉ በመበላሸታቸው ሳቢያ የማይተገበሩ ነበሩ፡፡ በ1839 አሜሪካዊው ፈልሳፊ ቻርለስ ጉድይር ያልተብላሉ ደቂቃንን ከድኚ (sulphur) ጋር በማቀናጀት ለተፈጥሯዊ ጎማ የቩልካናይዜሽን ሂደትን አገኘ፡፡ ይህ መሠረታዊ ሂደት ከተጨማሪ ኬሚካዊ አፋጣኞች እና አረጋጊዎች ጋር ዛሬም ጥቅም ላይ እየዋለ ነው፡፡ በ1945 ረጋ-ሠራሽ ጎማ ለገበያ ዋለ፡፡ የጎማ ፍላጎት እየናረ ስለመጣም ድፍን ጎማዎችን የሚተካ የውስጥ ቱቦን፣ ለጥንካሬ በተፈጥሯዊነት ወይም በረጋ-ሠራሽነት ተጠናክሮ የተገመደ ገመድን፣ እርጅናን ለመቀነስ ቁሶችን ማደባለቅ ጨምሮ ሌሎች መሻሻሎችም ታከሉ፡፡
፩. ኤነርጂ እና ማጓጓዣ ፩.6 ኤሮኖቲክስ የሙቅ-አየር ፊኛዎች (balloons) የመጀመሪያው ሰው ከክፍት ነበልባል በሚፈልቅ ሙቅ አየር በሚዘወር ፊኛ ውስጥ በ1783 በበረረበት ጊዜ የሙቅ-አየር ፊኛዎች ፈጠራ ስር-ነቀል ሆኖ ነበር የታየው፡፡ ሙቅ አየር ብዙም ሳይቆይ ለመቆጣጠር በሚቀልለው በሃይድሮጂን ተተካ፡፡ የሙቅ-አየር በረራ ተወዳጅ ስፖርት ከመሆኑ የተነሳ ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ብቻ ከ5,000 የሚበልጡ የሙቅ-አየር ፊኛ አብራሪዎች አሉ፡፡ ኬሚስትሪ ለዘላቂ፣ ለርካሽ እና ለሙቀት ተቋቋሚ ናይለን ፋብሪክ፣ ብሎም ለዝወራ ለሚጠቅመው ለፈሳሽ ፕሮፔን ቴክኖሎጂ አስተዋጽኦ አለው፡፡ ሂሊየም ዝና-ቢሱን ሂንደንበርግ (1937) የመሳሰሉት ሃይድሮጂን-ተሞይ ፊኛዎች ግትር መዋቅር ቢኖራቸውም እንኳን፣ የሃይድሮጂን ተቀጣጣይነት ሁልጊዜ የደኅንነት አደጋ የሚደቅን ነው፡፡ በ1905 ሁለት ኬሚስቶች ተፈጥሯዊ ሂሊየምን በአንድ የካንሳስ የጋስ ጉድጓድ ውስጥ ከአገኙ ወዲህ ነበር ይህ ብርቅዬ ኤሌሜንት በብዛት የታወቀው፡፡ በ፩ኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ከፍተኛ ብዛት ያለው ሂሊየም በኬሚካዊ ቴክኖሎጂ ይመረት፣ ይከማች እና ይላክ ነበር፤ በ፪ኛው የዓለም ጦርነት ጊዜም ሂሊየም-የተሞሉ የአየር-መርከቦች እና ለባሕር-ሰርጓጆች ለደኅንነት በወታደሮች የታጀበ አና በመርከብ የሚቀርብ ሂሊየምም ይላኩ ነበር፡፡ በ1950ዎች ውስጥ ሮኬት ሲገነባ እንደ መበየጃ እና የሮኬቱን ነዳጅ ወደ ሞተሮች ለሚገፋው እንደ ዘዋሪ ሂሊየም ጥቅም ላይ ይውል ነበር፡፡ የሂንደንበርግ ውድመት (1937) የሮኬት ነዳጆች በ1920ዎች ውስጥ ከተጀመረው ቀደምት የሮኬቶች ሙከራ አንስቶ እስከ የ1950ዎች የመገናኛ ሳቴላይቶች፣ የ1980ዎች ዳግም-ጠቃሚ የሕዋው ደርሶ-ተመላሽ መንኮራኩሮች ድረስ የሰው-ልጅ ወደ ሕዋው መስፋፋት ድንቅ የምሕንድስና ውጤት ነው፡፡ ስኬታማ የሕዋው ጉዞ የሚመካው ለምድር የስበት ኃይል በማይበገሩ ከፍተኛ የመጠነ-ፍጥነት (velocity) ግፊት ባላቸው ሮኬቶች ላይ ነው፡፡ የመጀመሪያው ሮኬት በ1926 የተመነጠቀው በቤንዚን ፈሳሽ ነዳጅ እና በኦክሲዳይዘር ፈሳሽ ኦክሲጂን በመጠቀም ነበር፡፡ ቀጥሎም የተለያዩ ነዳጆች እና ኦክሲዳይዘሮች በጠጣር ወይም በፈሳሽ መልክ ጥቅም ላይ ውለው ነበር፡፡ የሕዋው ደርሶ-ተመላሽ መንኮራኩር በፈሳሽ ሃይድሮጂን የሚጠቀም ይሁን እንጂ፣ የማምጠቂያው ሞተር እንደ ኦክሲዳይዘርየሚጠቀመው በአሉሚኒየም እና በአሞኒየም ፔርክሎሬት ጠጣር ፈሳሽ ነው፡፡ የአውሮፕላን እና የሮኬት መገንቢያ ቁሶች የአውሮፕላን ግንባታ ከእንጨት እና ከፋብሪክ ወደ ረቀቁ የምሕንድስና ቁሶች ሲሸጋገር ኬሚካዊ ቴክኖሎጂ ለቅያስ የሚፈለጉትን ቁሶች አቅርቧል፡፡ በአሉሚኒየም እና በቲታኒየም የተጠቀሙ የብረታ-ብረት ውህዶች የተሠሩት ለአውሮፕላን ጥንካሬ፣ ቀላል ክብደት፣ ከፍተኛ የሙቀት መረጋጋት እና የዝገት መቋቋም እንዲሰጡ ነበር፡፡ ሮኬቶች ደግሞ በሚንቀሳቀሱባቸው ጽንፍ ሁኔታዎች ምክንያት ልዩ የቁስ ፍላጎቶች አሏቸው፡፡ ለእዚህ አንዱ ምሣሌ የሕዋው መንኮራኩር (1980ዎች) ደርሶ ሲመለስ ከከፍተኛ መጠነ-ሙቀት የሚከላከለው የስልታዊ አጥቢያዎች ልዩ ንጣፍ ነው፡፡ ያልተለመደው ዚሮኮኒየም ኮምፖዛይት ቁስ ከተሞከረ በኋላ የመጨረሻው ንጣፍ ቅያስ የተሠራው ከተራ አሸዋ በተገኙት ሲሊካ ፋይበሮች ነበር፡፡